ዋና ገጽ

ኢብኑ ከሲር የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
مركز ابن كثير لتحفيظ القرآن الكريم
أديس أبابا – إثيوبيا

እንኳን ደህና መጡ

Where Your Donation Goes

  • Student Sponsorship (Highest Priority): Cover costs for a residential student (Food, Accommodation, Books, Tuition). Clearly state the monthly/annual cost per student. (👨🎓 Sponsor a Hafiz)

  • Educational Materials: Qurans, Islamic books, stationery, teaching aids. (📚 Equip a Learner)

  • Teacher Support: Stipends for qualified teachers. (👨🏫 Support a Teacher)

  • Facility Expansion & Maintenance: Building upkeep, utilities, future expansion projects (specifically mention the Quran College vision). (🏢 Build the Future)

  • General Fund: Where most needed to ensure smooth operations. 

0 +
ዙሮች አስመርቋል
0 +
አመታት ልምድ

ምስጋና ለዚያ መጽሓፍን በውስጡ ቅንጣት መጣመም (ግድፈት) ሳያደርግ በባሪያው ላይ ላወረደው አምላክ ይሁን፡፡ቀጥተኛ እና ግልጽ አድርጎ ላወረደው፡፡ከእርሱ የሆነን ብርቱ ቅጣት ሊያስፈራራበት እነዚያ በጎ የሚሰሩ አማኞችንም በመልካም ምንዳ በጀነት ሊያበስር አላህ ሱ.ወ የተገባው ነው፡፡ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያና ቁንጮ አድርጎ ለላካቸው በነብዩ ሰ.ዐ.ወ ላይ በባልደረቦቻቸው ላይ እንዲሁም የእርሳቸውን ፈለግ በቅን ለተከተሉ ሁሉ እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ ይሁን፡፡

  ኢብኑ ከሲር የቁርአን ሒፍዝ ማዕከል ከ1991 ጀምሮ በተመላላሽ የአካባቢ ተማሪዎች በማስቀራት ለፍሬ ያበቃ ሲሆን አድማሱን ለማስፋት ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ በአዳሪ መልክ ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ማስተማሩን ከጀመረበት በ2001ዓ.ል ብዛታቸው 30 የሚሆኑ ወንድ ተማሪዎችን ሁለት ክፍል ቤቶች ላይ መማሪያ፣ማደሪያ፣መመገብያ፣ቢሮ አድርጎ በተጣበበ ሁኔታ እያስተማረ ሳለ ለጉብኝት ወደ ማዕከሉ ጎራ ብለው በማዕከሉ እንቅስቃሴ የተደሰቱ የሀገራችን በጎ አድራጊ አህለል ኸይር ሐጂ አህመድ በሽር ለተማሪዎች ማደርያና ለማእከሉ ጠቅላላ ለአገልግሎት ስራዎች የሚሆን በ160 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ባለ ሁለት(2) ፎቅ ህንጻ በ2002 ዓ.ል መገባደጃ ላይ ግንባታው ተጀምሮ በ2003 ዓ.ል መጀመሪያ ላይ ሁለተኛው ዙር ተማሪዎችን ተቀብሎ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሳይገባደድ ስራው ቢጀመርም በአጭር ግዜ ውስጥ መጠናቀቅ በመቻሉ ቀድሞ ከነበረው የቅበላ አቅም እጥፍ በማሳደግ ብዛታቸው 65 የሚሆኑ አዳሪ  ወንድ ተማሪዎችን እንዲሁም ብዛታቸው 20 የሚሆኑ በተመላላሽ ተማሪነት የሚማሩ ሴት ተማሪዎችን በመቀበል ስራውን ቀጥሏል፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ሁለተኛው ዙር የተማሪዎች ቅበላ ግዜን የተሻለ ሁኔታ በማድረግ የቁርኣን ስርጭት ደካማ በሆኑባቸው አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ምልመላ የተደረገ ሲሆን ምንም እንኳ ለመሓፈዝም ሆነ የሒፍዝ ማእከላት ገብተው ለመማር ቁርአንን ቢያንስ እያየ መቅራት የሚችል ሰው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን እሙን ቢሆንም ቅድሚያ ለተደራሽነቱ  የሚለው መርሁ ከጠቅላላ ተማሪዎች መካከል ከአንድ አምስተኛ (1/5) ያላነሱ ተማሪዎች ቁርአንን እያዩ እንኳ ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎችን በመቀበል ትግሉን በማጠናከር ቁርአንን በነዘር (እያዩ ማንበብ) አስቀርቶ ወደ ሒፍዝ በማስገባት ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር አስተምሮ በአላህ ፍቃድ አስመርቋል፡፡በተጨማሪም በሶስተኛ፣በአራተኛ፣በአምስተኛ፣በስድስተኛና በሰባተኛ ዙርም እንዲሁ በርካታ  ወንድ እና ሴት ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአሁኑ ስምንተኛ ዙርም ወደ ማዕከሉ ከገቡ ወንድ ተማሪዎች መካከል ቁጥራቸው 90 የሚሆኑ ወንዶችን ለምረቃ አብቅቷል፡፡በዚህም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎችን አጠቃላይ ወጪ ሲሸፍን የነበረው ከተለያዩ አህለል ኸይራት ድጋፍ በማሰባሰብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ከሁለተኛው ዙር ቅበላ ጀምሮ የማዕከሉን ሙሉ ወጪ  ሕንጻውን ባስገነቡት በጎ አድራጊ የሚሸፈን በመሆኑ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚደረገውን ሃሳብና ድካም በማስቀረቱ ሙሉ ትኩረቱን በማስተማር ላይ በማድረጉ ከበፊቱ በተሻለ መልኩ የትምህርት ጥራት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ አስችሎታል፡፡ ተማሪዎች በማዕከሉ ቆይታቸው ከቁርአን ሒፍዝ ጎን ለጎን መሰረታዊና ለጀማሪ የሚሆኑ የዲን ትምህርቶችን የቀሰሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ተጅዊድ፣ዓረብኛ ቋንቋ፣ሐዲስ፤ተውሂድ፣ኡሉመልቁርአን፣ፊቅህ፣ሲራ እና አዳቡ ጣሊበል ዒልም እንዲሁም የተለያዩ የተርቢያ ትምህርት ዋና ዋና  ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ተመራቂ ተማሪዎች ላይ በሚያደርገው ክትትልም ከፊሉ ሙሉ በሙሉ ዒልም ፍለጋ ጊዜያቸውን የሰጡ ቢሆንም ገሚሱ ተማሪዎች በየሄዱበት ሐገራት አካዳሚክ ትምህርታቸውን እየተማሩ ቁርአንን በማስተማር ላይ እንዳሉ እና ሌሎችም  በኢማምነት በየአካባቢያቸው እያገለገሉ፤ በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት እያካሄዱ ሲሆን በዋናነትም ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ በመስጠት በአዳሪ መልክ ተማሪዎችን ይዘው እያስተማሩ ይገኛሉ፡፡ በሃገራችን እየታየ ያለው የቁርአን ተህፊዝ እምረታ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ካለው ሙስሊም ህዝብ ብዛት ጋር ሲነጻጸር ከ1 ፐርሰንት የተሻገረ እንቅስቃሴ ሆኖ አናገኘውም፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ይህን ታላቅ ስራ በየመስጂዱ  እና ቁርአን ማቅሪያ ቦታዎች ላይ በማቋቋም በቀላል ወጪ በጧትና ማታ ፕሮገራሞች ብቻ ብዙ መስራት የሚቻል በመሆኑ የአኺራ ወንድምና እህቶች ሁሉ አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደምንችል ማስታወስ እንሻለን፡፡ ኢብኑ ከሲር የቁርአን ሒፍዝ ማዕከልም እስከ ቁርአን ኮሌጅ የማቋቋም ህጋዊ ፍቃድ ያለው ቢሆንም ባለው አቅም ውስንነት ምክንያት አሁን ባለው ሁኔታ የተገደበ በመሆኑ ኸይር ፈላጊ ወንድሞች በሙሉ ከሚመለከታቸው የማዕከሉ ሐላፊዎች ጋር በመወያየት የዚህ ታላቅ አላማ ተቋዳሽ እንድትሆኑ አበክረን በዚሁ አጋጣሚ ወንድማዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ እስካሁን ማእከሉ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ያላሰለሰ ጥረትና አስተዋጽኦ ያደረጋቹ ሁሉ በተለይም አባታችን ሐጂ አህመድ በሽርን አላህ ከፍ ያለውን ደረጃ  እንዲሰጣቸው እየተመኘን ማእከሉ ዘርፉን ለማጠናከር በሚያደርገው ትግል ከመቼውም ግዜ በተሻለ መልኩ መበርታት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ታላቅ ስራ አላህ ሱ.ወ በሰጠን ሁሉ መሳተፍ ወሳኝ ተግባር መሆኑ እሙን ነው፡፡ ስለሆነም በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ ውድ የአኺራ ወንድምና እህቶች ሁሉ ጥሪያችን ዳግም እያስተላለፍን አላህ ሱ.ወ ቅኑን መንገድ እንዲመራን እየተማፀንን የእርሱ ቃል የሆነው የቁርአን ቤተሰብ እንዲያደርገን እንለምነዋለን፡፡

  • የቁርአን ኮሌጅ መቋቋም

  • የተደራሽነት ዘርፍ ማስፋፋት

የቁርአን ሂፍዝ
መሰረታዊ የዲን ትምህርቶች
የወንድ ተማሪዎች ማደሪያ እና መመገቢያ
የሴቶች ተመላላሽ የሂፍዝ ፕሮግራም

የማዕከሉ አመራሮች

ኡስታዝ መሐመድ አብዱልቃድር

ዋና ስራ አስኪይጅ

አጭር ገለጽ ስለ ኡስታዝ

ኡስታዝ አሚር ሰዒድ

ም/ስራ አስኪያጅ

አጭር ገለጽ ስለ ኡስታዝ

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ም/ስራ አስኪያጅ

አጭር ገለጽ ስለ ኡስታዝ

Latest News

Contact

+251996407373

ይደዉሉ
Location
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ሸይኽ ሆጀሌ መስጅድ ቅፅር ግቢ
Email
ikmibnukathir@gmail.com